ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 49 (Zehabesha Newspaper # 49) – PDF
የኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ዜና ምንጭ ወያኔ ነው
በርካታ የኤርትራና አፍቃሪ ህወሀት/ኢህአዴግ ብሎጎች፣ የህወሀት/ኢህአዴግ ደጋፊ ካድሬዎች እንዲሁም የተቃዋሚ ደጋፊ መስለው የሚንቀሳቀሱ ድረ-ገጾች በአንድላይ “መንግስቱ Mengistu_Haile_Mariam ሀይለማርያም አረፈ” የሚል ዜና በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ ጉዳዩን አንድም ነብስ ያለው የዜና አውታር አልዘገበውም።
ይህን አስመልክቶ ታዋቂው የኢሳት ራድዮ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የሚከተለውን በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል፣
ኮነሬል መንግስቱ ኃይለማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ፌስቡኩን ድረ-ገጹን የወረረ ምንጭና ፍንጭ የሌለው ወሬ በግሌ ወረርሽኙ ሲዛመት ለማጣራት ያሉኝን መንገዶች በሙሉ ተጠቀምኩ ደወልኩ ነዘነዝኩ ምንም የለም ሊንክ ተደርገው የተለጠፉና ምንጭ ተብለው የተጠቀሱትን በሙሉ አየሁ በረበርኩ ዋንኛ ምንጭ የተባለው ድረ ገጽ ከሶስት ሳምንት በፊት የለቀቀውና ውሸት መሆኑ ወዲያውኑ ኢሳት ያረጋገጠው ነበር ሌላው የዙምባቡዌ ቴሌቪዥን ተናገረ የተባለው ነው ሲከፈት ግን ምንም የለም እና ወሬው ከየት መጣ የበዓሉ ግርማ በህይወት አለ ወረርሽኝ ለማንኛውም እስከዚህ ሰዓት ድረስ ባለኝ መረጃ ኮነሬል መንግስቱ ኃይለማያም በህይወት አሉ።
ሀና መታሰቢያ በመባል የምትታወቅ የፌስቡክ ተተቃሚ ደግሞ እንዲህ ብላለች፣
ፌስቡክን ሙሉ ለሙሉ መዝጋት ፖለቲካል ኪሳራው ከባድ መሆኑን የተረዱ የሚመስሉት ወያኔዎች ከዚህ ይልቅ ለየት ያለ መንገድ እየተከተሉ ነው።ፌስቡክ ውስጥ እየተፈጠሩ ያሉት አባዛኛዎቹ አሉባልታዎች ምንጭ ወያኔዎች ይመስሉኛል። በአጠቃላይ ፌስቡክን በተመለከተ የወያኔ ፕሮፐጋንዲስቶች እየተከተሉ ያሉት መንገድ፦
1. ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸውን ግሩፖችና ገፆችን ነጥሎ መዝጋት(ምንም እንኳን በhttps://መከፈት ቢችሉም)
2. ፌስቡክ ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ ግለሰቦችን አካውንት መዝጋት
3. መንግስትን የሚያወግዙ ፖስተሮችና ፅሑፎች ስር ከርዕሱ ባፈነገጠ መልኩ ፖስት ያደረገውን ግለሰብ በመዝለፍ የውይይቱን አቅጣጫ ማሳት
4. ፌስቡክ ላይ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ ግለሰቦችን ሜሴጅ እየላኩ ማስፈራራት፣ በስድብና በዛቻ ማሸማቀቅ
5. ምንም እንኳን ማንኛውንም ነገር ያለ ፕሮግራም መጠቀም ጊዜን ማባከኑ እሙን ቢሆንም ወያኔዎች ስለፌስቡክ ጊዜ አጥፊነት የሚሰብኩት ለኛ በማዘን አይደለም ስለሚጠፋ ጊዜ ከምር ቢጨነቁ ሀገሪቷን የወረሯትን ጫት ቤቶች በዘጉ ነበር እስካሁን የፌስቡክን ጉዳት እና ጊዜ አጥፊነት በተመለከተ በወያኔ ሚዲያዎች ከ3 ጊዜ በላይ ፀረ ፌስቡክ ዝግጅቶች ቀርበዋል
6. አዲሱ የወያኔ ፕሮፐጋንዲስቶች ታክቲክ መያዣ መጨበጫ የሌላቸውን አሉባልታዎች በፌስቡክ በመንዛትና በማሰራጨት የፌስቡክን ተአማኒነት በመቀነስ ፌስቡክ የቦዘኔዎች ብቻ መሰብሰቢያ የሚመስል ገፅታ እንዲላበስ ማድረግ በዚህ መንገድ ከተነዙ አሉባልታዎች ውስጥ የልመንህ ሞት፥ የበአሉ ግርማ በህይወት ተገኘ መባል እና የዛሬው የመንጌ ሞት ይጠቀሳል።
እኛ ጭቁን ኢትዮጵያውያን ጉዟችን እሩቅ ነውና በጅላጅል አሉባልታዎች ሳንዘናጋ ፌስቡክን እንደ መወያያ እና መገናኛ መድረክ እንጅ እንደዋነኛ የትግል አውድ ሳንወስድ ትግላችንን እናበርታ።
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 50 – PDF
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 51 (PDF)
(ለማንበብ የጋዜጣው ሽፋን ገጽ ላይ ይጫኑ)
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 52 – PDF
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 53 – PDF
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 54 (PDF)
Zehabesha Newspaper: ዘ-ሐበሻ በቁጥር 56 ዕትሟ ምን ይዛለች? (PDF)
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 58 – PDF
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 58 የዲሴምበር 2013 ዕትም ወጥቷል። እንደሚታወቀው ዘ-ሐበሻ ዲሴምበር 28 5ኛ ዓመቷን ትደፍናለች – እንኳን አደረሰን።
በዚህ በ2013 የመጨረሻው ዕትማችን ላይ የያዝናቸውን ቁምነገሮች እናስቃኛችሁ እና በPDF ፎርማት ሙሉውን ጋዜጣ ፕሪንት አድርጋችሁ ማንበቡን፤ ወይም በዲስክ ቶፕ ላይ ሴቭ አድርጋችሁ መኮምኮሙን ለናንተ ትተናል። በሚኒሶታ እና አጎራባች ስቴቶች ያላችሁ ጋዜጣዋን በነፃ በኢትዮጵያውያን ንግድ ቤቶች ማግኘት ትችላላችሁ።
- $44,000 ይላል አብይ ርዕሳችን። በሚኒሶታ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲን ሕንፃ ለመግዛት በተደረገ የገቢ ማሰባሰብ ምሽት በአንድ ቀን 44,000 ዶላር ተሰብስቧል። በዚህ ዙሪያ ሰፊ ዘገባ አለን። ኢትዮጵያዊነት በሚኒሶታ ከፍ ያለውን ቦታ እየያዘ ነው።
- የአትላንታው የዘ-ሐበሻ ወኪል ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወየሳ ኢሕአዴግ በኦጋዴን ስላከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን በተመለከተ ያሰናዳው ጥልቅ ዘገባ በዓብይ ርዕሳችን ይዘነዋል።
- “በየወሩ መልዕክቴን በዘ-ሐበሻ በኩል የማስተላልፈው ራዕይ ታይቶኝ ነው” ትላለች ፓስተር ደስታዬ። ይህን ለምን እንዳለች ያንብቧት።
- የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን በማሰጠትና ለዜጎች ሞት የሚጠየቁት አቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣናቸውን ለቀቁ
- ኔልሰን ማንዴላ እና ኢትዮጵያ!!ተጨማሪ ማስታወሻዎችና ከኢትዮጵያ የወሰዱት ሽጉጥ መጨረሻ በጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወየሳ – አዳዲስ መረጃዎችን ስለ ማንዴላ ያቀብላችኋል።
- ዘ-ሐበሻ ሁሌም በምትወደስበት የጤና አምዷ
* የተወሰኑ የነቀርሳ ዓይነቶችን በኤችፒቪ ክትባት አማካይነት ይከላከሉ (MDH እና zehabesha በመተባበር ያቀረቡት ትምህርታዊ ዘገባ)
* በተለይ በበረዷማ ከተማዎች ውስጥ ለምትኖሩ የቫይታሚን ዲ ምስጢሮች /The Secret to Boosting Vitamin D Levels All Winter (ሊያነቡት ይገባል)
* ቦርጭን ማጥፊያ የምግብ ዓይነቶች
* የሐሞት ጠጠር ጉዳይ! ተተንትነዋል።
በሴቶች ጤና አምዳችን ደግሞ፦
* የሊሊ ሞገስን የማረጥ ዕድሜ ለውጦችሽን የምታስተናግጂባቸው 19 ምርጥ ጥበቦች (Menopause (Perimenopause) Symptoms,Treatments, Diet …)
* የ’ፍንዳታው’ አንጎል (በንዮሳይንስ መጽሔት ላይ የቀረበውን የባለሙያ ትንታኔ ተርጉመን ይዘነዋል)
በሃኪምዎን ያማክሩ (እንመካከር አምድ) ለ4 ጉዳዮች ምላሽ አግኝተናል
* “ባለቤቴ እንደምትወደኝ አውቃለሁ፤ የወሲብ ፍላጎት ግን የላትም፤ በዚህ የተነሳ ትዳሬ አደጋ ላይ ነው” – ምላሽ ይዘናል
* ለጨጓራ መላጥ (አልሰር) በሽታ መፍትሄው ምንድን ነው?
* እግሬ ላይ ጋንግሪን ሊወጣ ነው ወይ?
* ነጭ ጓደኛ ይዤ ፍቅር መስራት ጀመርን። ወዲያውኑ ብልቴ አካባቢ ያሳክከኝ ጀመር፤ ቢጫ ሽንት አየሁ” – ለዚህም የባለሙያ ምላሽ አለን።
በወንጀል ነክ ዜናዎቻችን፦
* በአሪሲ የ11 ወሩን ሕጻን ብልት የቆረጠች እናት 10 ዓመት ተፈረደባት
* የ3 ዓመት ሕፃን በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው 6 ዓመት ተፈረደበት
በስፖርት አምዳችን 3 ጉዳዮችን ይዘናል፦
* 4-1-3-1-1 ወይም 3-2-3-2 ወይም 3-3-3-1 1-1-3-1-1 ወይም 1-4-3-2 የማንችስተር ዩናይትድ ታክቲካዊ አማራጮች
* “ኢትዮጵያን አሸንፈን ለዓለም ዋንጫ በማለፋችን የቼልሲ ተጨዋቾች ደስታቸውን ገልፀውልኛል›› – ኬኔት ኦሜሮ (Kenneth Omeruo)
* የአርሰናሉ ሮዚስኪ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? ያንብቧቸው።
- በሳይኮሎጂ አምዳችን ላይ ለደስተኛ ሕይወት 25 ምርጥ ምክሮች አሉን ይማሩባቸዋል ብለን እናስባለን።
በጥበብ አምዳችን፦
* “ትወና መምሰል ብቻ ሳይሆን መሆንም ጭምር ነው” መሐመድ ሚፍታህ (ፋርማሲስት፣ ተዋናይ፣ የማስታወቂያ ባለሙያና የፊልም ፕሮዲዩሰር) ቃለ ምልልስ ይዘናል።
* ስለ አስቴር አወቀ ወደ ሚኒሶታ መምጣትም ዘገባ አለን።
ምን ይሄ ብቻ፡ ግጥሞች፣ አዝናኝ ጽሁፎች፣ ስለ አሜሪካ ኑሮ፣ ማስታወቂያዎች፣ የተለያዩ መረጃዎች የቁጥር 58 አካል ናቸው።
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 59 – PDF
እዚህ ይጫኑ
6ኛ ዓመቷን የጀመረችው ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ የጃንዋሪ ዕትም እነሆ ወቅቷን ጠብቃ ወጥታለች።
ዘ-ሐበሻ በቁጥር 59 ዕትሟ የያዘቻቸውን ቁምነገሮች እናስቃኛችሁና ሙሉውን ዘገባ ለPDF እንተወዋለን።
* በፊት ለፊት ገጻችን ላይ “ሌንጮ ወደ ፊንፊኔ” የሚል ዘገባ ያነባሉ። በዘገባው ከፍተኛ የኦሮሞ ኮምዩኒቲ በሚገኝባት ሚኒሶታ በነሌንጮ ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ውሳኔ ዙሪያ ያላቸውን ሃሳብ ያዩበታል።
* “በአጼ ምኒልክ ዙሪያ ሰሞኑን እየተወራ ስላለው ነገር ቴዲ አፍሮ “እኔ ቅዱስ ጦርነት ነው ብዬ አልተናገርኩም” ይለናል – ዘገባ አለን።
* የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች እየደወሉ ስለ አዲሱ የአሜሪካ የጤና ፖሊሲ ወይም ኦባማ ኬር ምን የምትሉን አለ? ሲሉን ቆተዋል፤ እኛም ከደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ የፓሪሽ ነርሶች ማህበርና ዩኬር ጋር በመተባበር ያዘጋጀነው ትምህርታዊ ዘገባ ተይዟል።
* የሚኒሶታ ነዋሪ ከሆኑ ጥሩ የመዝናኛ ዜና አለን፦ ድምፃዊት አበባ ደሳለኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ሚኒሶታ በመምጣት ዘፈኖቿን ታቀርባለች
* ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ከአምስተርዳም “በአንድ ጋዜጠኛ ስህተት በወጣ ጽሁፍ ስንሟገት ዋናውን ጉዳይ እንዳንረሳ” ይለናል፤
* ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ ስለ ምኒልክ ይናገራሉ
* በጤና ጉዳይ በሚመካከረው “እንመካከር” አምዳችን 4 ጉዳዮችን መርጠን ተንትነናል
- “ከእርሱ ጋር አብረን መሆኑ ያማል፤ ጨርሶ ከእርሱ መራቁም ከብዶኛል”
- ከድብርት ለመላቀቅ ወሲብ ማድረግ ቢነገረኝም እርሱም አልረዳኝም
- የጨጓራ ህመሜ ወደ ካንሰርነት ተቀይሮ ይሆን?
- በአንገቴ ዙሪያ ያለው ዕጢ ምን መፍትሄ አለው? የሚሉ ጉዳዮች ተይዘዋል::
በወንጀል ዜናዎች፦
* ሙሽራዋን የገደለው እድሜ ልክ ተፈረደበት
* ሴተኛ አዳሪዋን ገድሎ በጆንያ ሊጥል የነበረው ክስ ተመሰረተበትሚሉ ዘገባዎችን ይዘናል
በጤና አምዳችን፦
* ስለቶንሲል ቆንጅዬ ዘገባ ይዘናል
* አጃ ለጤና ያላትን ጥቅም ማወቅ ይፈልጋሉ? ገጿን ገልበጥ ገልበጥ ያድርጉ
* ስለራስ ወዳድነት አንድ ስነልቡናዊ ዘገባም ይዘናል “ታመው ዞር ብለው ላላይዎት ልጆችዎ ንብረትዎን ያወርሳሉ ወይ?”
* አስደናቂ ጤና ነክ 40 እውነታዎች
* የዕለት እንጀራችንን እንደየደም ዓይነታችን
በሳይኮሎጂ አምዳችን፦
* ጠንቋይ መሆን ይፈልጋሉ? – እንግዲያውስ ቢያንስ የራስዎ ጉዳይ ጠንቋይ መሆን ይችላሉ (ምርጥ ዘገባ ያንብቡት)
* ከስራ ሊያስባርርዎ የሚችሉ ምክንያቶች
በስፖርት አምዳችን፦
* ማን ዩናይትድን ምን ነካው?
* የአርሰናሉ ኦዚል ይናገራል
* የባርሴሎና ተጫዋቾች ደካማና በመልካም ሁኔታ የሚገኙትን የስፖርት ተንታኞች ፈትሸዋቸዋል – ይዘነዋል።
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 60 – PDF
በሰሜን አሜሪካ ትልቋ የኢትዮጵያ ጋዜጣ ዘ-ሐበሻ እነሆ ቁጥር 60 ለንባብ በቅታለች።
እንደተለመደው በውስጧ የያዘቻቸውን ቁምነገሮች እፍታውን እናጨብጣችሁና ንባቡን ለናንተው እንተወዋለን።
* ዓብይ ትኩረታችን ያደርግነው በአውሮፕላኑ ጠለፋ ዙሪያ ነው። የተለያዩ ጉዳዮች ተዳሰዋል።
- ከአውሮፕላኑ ጠለፋ ባሻገር የፖለቲካ ይዘት አለው
- አውሮፕላኑን የጠለፈው ኃይለመድህን አበራ ተገኝ ማን ነው?
- የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የዜጎች እኩልነት አለመረጋገጥ፣ በሥራ ቦታ ላይ ነጻነት ማጣት፣ የኢኮኖሚ ችግር፣ የነፃነት እጦት አውሮፕላኑን አስጠለፈው
- የረዳት ፓይለቱ ድርጊት የአፈናው ውጤት?
- የኢትዮጵያ ነገርና – የአብራሪው ጉዳይ የሚሉ ወቅታዊ ዘገባዎችን ይዘናል።
* በወሩ ታላቅ ዜና አምዳችን፡ የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ “ኢትዮጵያዊነት-”የለህም ይሉኛል፤ እውን የለህም ወይ?” በሚል የፃፈውን ወቅታዊ ትንታኔ ይዘንላችኋል።
* ከሚኒሶታ የጤና ማዕከል ጋር በመተባበር በምናቀርበው አምዳችን ‘ስለ ክትባቶች እና ስለ እርግዝና ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች” የሚል ትንታኔ ይዘናል፤ ቢያነቡት ይጠቀማሉ።
* አዲሱን የNYPD (የኒዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት) ስማርት ካር ውስጡ ምን እንዳለው ሰምተዋል? – ሊያመልጥዎ አይገባም።
* በሕይወት በአሜሪካ አምዳችን፡ ሥራ ፍለጋ ኢንተርኔት ገብቼ ፌስቡክ ላይ ተሰጥቼ እውላለሁ የሚል ትዝብታዊ ጽሁፍ አካተናል።
* ተወዳጁ ድምፃዊ ብርሃኑ ተዘራ (ያምቡሌ) በሚኒሶታ ሥራዎቹን ማርች 15 ያቀርባል
* ዲያቆን ዳንኤል ክብረት “የመረረው አብዮተኛ (ለ1966ቱ አብዮት 40ኛ ዓመት ማስተዋሻ)” በሚል የፃፈው መጣጥፍም የቁጥር 60 ዕትማችን አካል ነው።
በወንጀል ዜና አምዳችን፦
- 3 ልጅ የወለደችለት ሚስቱን በጥርጣሬ የተነሳሕይወቷን አጠፋ
- በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ የታክሲ ሾፌሩን ተሳፋሪው ገደለው የሚሉ ሁለት ዜናዎችን ይዘናል ትንታኔ አላቸው።
በእንመካከር አምድ 4 ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።
- “ከባለቤቴ ጋር ስምምነት መፍጠር ተሳነኝ፤ እባካችሁ አንድ በሉኝ”
- ከድብርት ለመላቀቅ ወሲብ ማድረግ ቢነገረኝም እርሱም አልረዳኝም
- ጉሮሮዬ ከተዘጋ 10 ዓመት ሆነው
- በዱካክ ተሰቃየሁኝ፤ ምን መፍትሄ አላችሁ? ምላሾቹን ያንብቧቸው፤ ይማሩባቸዋል።
* በጤና አምዳችን 3 ጉዳዮች እንደተለመደው ተካተዋል።
- ፕሮቴስት የወንዶች ብቻ ችግር (ወንዶች ልብ ብላችሁ አንብቡት)
- ትራኮማ እና የዓይን ሞራ ግርዶሽ
- የነስር ነገር – Epistaxis ፦ ለምን ይነስረናል? የሚሉ 3 ምርጥና አስተማሪ ዘገባዎችን አካተናል ያንብቡን።
* በሴቶች አምድ፡ ማስካራ ትጠቀሚያለች? እንግዲያውስ ይህን አንብቢ ትለናለች ሊሊ ሞገስ፤ ያንብቡላት።
* በሳይኮሎጂ አምዳችን፤ ቅናት ለፍቅር ምኑ ነው? የሚል ቆንጆ ዘገባ አለን።
* በስፖርት አምድ እንዳስለመድነው 3 ጉዳዮች አሉን።
- ፍሌቸር በቀን እስከ 30 ጊዜ መጸዳጃ ቤት ይመላለስ ነበር
- ማርቴሳካር፡ ግዙፉ ጀርመናዊ
- ጋሪ ኩክ የማንቸስተር ሲቲው አዳኝ
በዘ-ሐበሻ ቁጥር 60 ላይ እነዚህ ብቻ አልተካተቱም፤ በርከት ያሉ ዘገባዎች ከማስታወቂያዎች ጋር ታጅበው ቀርበዋል። ያንብቡ።
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 61 – PDF
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 61 ወጥታለች። በሚኒሶታ የምትኖሩ ከ92 በላይ ቦታዎች ላይ ጋዜጣችን ስለተቀመጠ ማግኘት ትችላላችሁ። በውጭ ያላችሁ ደግሞ በPDF አቅርበንላችኋል።
* ከሚኒሶታ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ እየሆነ የመጣው የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ ዓብይ ር ዕሳችን ነው። ጉዳዩ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ተሸጋግሯል፤ ብዙሃን በጉጉት ሲጠበቁት የነበረው ጠቅላላ ጉባኤም ተጠርቷል።
* የተመስገን ደሳለኝ አዲስ ጽሁፍ “ኑ እንዋቀስ! ኢሕ አዴግን እናፍርሰው” የጋዜጣችን አካል ሆኗል
* የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ እንዴት በምግብ መመረዝ ሊሞቱ ይችላሉ? – አንድ የህክምና ባለሙያ በምግብ መመረዝ የተነሳ የሚከሰቱ 4 በሽታዎችን ይዘውልናል – ያንብቡት።
* በቀድሞው ጦቢያ መጽሔት ላይ ተወዳጅ ብ ዕሩን የምታነቡለት ጸጋዬ ገብረመድህን አረአያ “የመስዋዕትነት ወንጌል” የሚል ጠንካራ ዘገባ አድርሶናል – ያንብቡት።
በእንመካከር አምዳችን፡ 3 ጉዳዮች ተይዘዋል።
* “ፍቅረኛዬ በወሲብ ወቅት ተቃጠልኩ፤ አሳመምከኝ እያለች አስቸገረችኝ”
* ትዳር የሚመሰርቱት ምን ዓይነት ፍቅረኞች ናቸው?
* ሰዎች “ውስጣዊ ውበት እወዳለሁ” ሲሉ እሰማለሁ ምንድ ነው? ለሚሉት የባለሙያ ምላሾችን ይዘናል።
በአሜሪካ ጉዳይ አምዳችን፦
* ቤትዎ ከመሸጡ በፊት ከመንግስት በሚያገኙት ዕርዳታ ማትረፍ ይችላሉ ይለናል የጠበቃ ሳምሶን በዙ ጽሁፍ። ቢያነቡት ይጠቀማሉ።
* በሰሜን አሜሪካ ሁካ (ሺሻ) በጣም እየተለመደ የመጣ ነገር ሆኗል። ለመሆኑ ሁካ ምን ይጠቅማል? ምን ይጎዳል? የሚል አስተማሪ ዘገባ ይዘናል። ለጤናዎ የሚያስቡ ከሆነ ያንብቡት።
እንደተለመደው በጤና አምዳችን 3 ጉዳዮችን ይዘንላችኋል።
* ምን ልብላ? What Should I Eat?
* የማደንዘዣ ቴክኒክ ምስጢር፤ ከህሊናችን ስንርቅ የት እንገባለን?
* ኢንዶስኮፒ ለማን እና ለምን? – ያንብቧቸው።
ለእረፍትዎ አምዳችን ላይ 2 ጉዳዮች ተይዘዋል።
* የጆሮ፣ አፍንጫና ጉሮሮ አስገራሚ ወዳጅነት
* ሰዎች ከእንስሳ ሊለዩ የሚችሉባቸው 15ቱ ልዩ ዘዴዎች
በስፖርት አምዳችንም 3 ጉዳዮች ተስተናግደዋል።
* የዓለም ዋንጫ እየተቃረበ ቢሆንም የጀርመን አቋም አሳሳቢ ሆኗል፤
* ስለማን.ሲቲ፣ባርሴሎና እና እንግሊዝ ዣቪ ይናገራል
* ቲያጎ የባርሴሎናው ዣቪ አልጋ ወራሽ – ይዝናኑባቸው።
በሴቶች ጤና አምዳችን ሴቶችን በብዛት ስለሚያጠቃው የኩላሊት ኢንፌክሽን ላይ ጥሩ ዘገባ አቅርበናል።
ምን ይሄ ብቻ?
የዲ/ን ዳንኤል ክብረት፣ የኤፍሬም እሸቴ፣ የዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳን ጨምሮ ሌሎች አዝናኝና አስተማሪ ዘገባዎችን ከማስታወቂያዎች ጋር አጅበን ይዘናል። ያንብቡን።
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 65 (PDF)
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 67 – PDF
ዘ-ሐበሻ –መጋቢት 2007 ቅጽ VI ቁጥር. 72
– የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ሚኒሶታ ሊመጣ ነው- የወያኔን የእብሪት ወረራ እስከመቼ እንሸከማለን?
ዘ-ሐበሻ – መጋቢት 2007 ቅጽ VI ቁጥር. 72
The post ዘ-ሐበሻ – መጋቢት 2007 ቅጽ VI ቁጥር. 72 appeared first on Zehabesha Amharic.
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 73 – PDF
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 74 (በPDF ያንብቡ)
የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ልደት በማስመልከት የታተመ ልዩ ጋዜጣ –መዲና (PDF)
በሃገር ቤት የማሳትማት መዲና ጋዜጣና መጽሔት በ1995 በኢትዮጵያ አቆጣጠር የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ልደት በማስመልከት ልዩ ዕትም ጋዜጣ አዘጋጅታ ነበር:: ከጋዜጣውም በተጨማሪ ልደታቸውን በኢምፔሪያል ሆቴል አክብረን ነበር:: በዚህ 12 ገጾችን በያዘው ጋዜጣ ላይ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሕይወትን ለመዳሰስ ሞክረን ነበር:: ይህን መዲና ጋዜጣ ከ10 ዓመታት በኋላ በአሜሪካው ኮንግረስ ላይብረሪ አግኘሁት:: ዛሬ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ 123ኛ ዓመት የልደት በዓላቸው በመሆኑ ይህን ጋዜጣ በፒዲኤፍ ታነቡት ዘንድ ጋብዣለሁ::
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 77 (PDF)
ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ – 78 (PDF)
በሰሜን አሜሪካ ትልቁ የኢትዮጵያውያን ጋዜጣ የሆነችው ዘ-ሐበሻ የ8ኛ ዓመት ጉዞዋን ልትጀምር ነው:: እነሆ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ በ32 ገጾች መረጃዎችን ይዛ በሚኒሶታና አካባቢው በሁሉም የኢትዮጵያውያን እና የምስራቅ አፍሪካ ንግድ ቤቶች ውስጥ ተቀምጣለች:: በዓለም አቀፍ ደረጃ በድረገጻችን ለምታነቡንም በፒዲኤፍ (PDF) ይዘንላችሁ ቀርበናል::
ዘ-ሐበሻ – እውነት ያሸንፋል